በሥራና ክህሎት ሚንስቴር በቀረበው የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ጥቅም አስጠብቆ በማሰማራት በተከናወኑ ተግባራት ትልቅ ስኬት መመዝገቡ ይታወቃል። አሁንም በዚሁ ህጋዊ የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት በተለያዩ የሞያ ዘርፎች 3000 የሰው ሃይል ይፈለጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የሞያ ዘርፎች ሞያተኛ የሆናችሁ በሙሉ በዚህ ልዩ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
የሥራ ቦታ: የተባበሩት አረብ መንግስታት /UAE/የኮንትራት ቆይታ: ሁለት አመት ተፈላጊ ፃታ: ወንድበተዘረዘሩት እያንዳንዱ ሞያዎች ከ250 እስከ 1000 ሰው በጥቅሉ 3000 ሰው ይፈለጋል።
የሞያ ዘርፎች:-1- Mason (block & plaster)/ ግንበኛ (የብሎኬት እና የልሰና ሰራተኛ)2- Steel fixer/የብረት ሙያተኛ/3- Shuttering Carpenter /የሸተር ሰራተኛ/አናጺ/4- Electrician /ኤሌክትሪክ ባለሙያ/5- Plumber /ቧንቧ ሰራተኛ/6- Fitter/መካኒክ / የማሽን አቀናጅ ባለሙያ/7- Technician /ቴክኒሺያን/
የምትመዘገቡበትን ስልክ ቁጥር ከአንድ ጊዜ በላይ በመጠቀም ፎርም መሙላት እንደማትችሉ እያስታወቅን ከአንድ ጊዜ በላይ የሚጠቀም ሰው ማመልካቻውን ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንደምናደርግ ልናሳስብ እንወዳለን። ማንኛውም መረጃ ለመጠየቅ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ነጻ የስልክ መስመር 9138 ይደውሉ።